የዳያስፖራ አባላት በአፋር ክልል እየለማ ያለ የቆላ ስንዴ ማሳ ጎበኙ

130

ታህሳስ 25 ቀን 2014 (ኢዜአ) የዳያስፖራ አባላት በአፋር ክልል እየለማ ያለ የቆላ ስንዴ ማሳ ጎበኙ።

የእናት አገር ጥሪን ተከትሎ ወደ አገር ቤት የገቡ ዳያስፖራዎች በክልሉ የሚገኙ የእርሻና የቱሪዝም ልማት ፀጋዎችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸውም በአፋር ክልል በመልሶ ግንባታው ከሚያደርጉት ድጋፍ ባለፈ በክልሉ መዋዕል ነዋያቸውን ለማፍሰስ አማራጮችን እንደተመለከቱ ገልፀዋል።

ከጎበኙት የቱሪስት መስህብ መካከል ከሰመራ በስተደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ የሚገኘው የአላሎባድ የተፈጥሮ ፍል ውሃ ይገኝበታል።

በትናትናው እለት ወደ ስፍራው ያቀኑ በርካታ ዳያስፖራዎች የተሳተፉበት የዳያስፖራ ሲምፖዚየም በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ዛሬ መካሄዱ ይታወቃል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም