ከፍተኛ አመራሮች በድህረ ጦርነት በሚኖሩ ሂደቶች ላይ እየተወያዩ ነው

180

ታህሳስ 25 ቀን 2014 (ኢዜአ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከፍተኛ አመራሮች በድህረ ጦርነት በሚኖሩ ሂደቶች ላይ ውይይት እያካሄዱ ነው።

የክልሉ መንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞ ለኢዜአ እንደገለጹት ውይይቱ እየተካሄደ ያለው በክልሉ ሦስት ከተሞች ነው።

“በዘላቂ ድል ወደ ብልፅግና” በሚል መሪ ሀሳብ በቦንጋ፣ሚዛን አማንና ተርጫ ከተሞች እየተካሄደ ባለው ውይይት የወረዳና የዞን ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ መሆኑን ተናግረዋል።

ውይይቱ ከህልውና ከጦርነት በኋላ መደረግ ስላለባቸውና በፍጥነት መስተካከል የሚገባቸው ሁኔታዎችን በመለየት የጋራ ግንዛቤ ይዞ ወደ ተግባር ለመግባት ታስቦ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለው ድል የመላው ኢትዮጵያውያን አሻራ መሆኑን አመልክተው ድሉ ዘላቂ ሆኖ ወደ ብልጽግና የሚደረገውን ጉዞ ማፋጠን እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ

‼️

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼️

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼️

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼️