ተቋማቱ ለተፈናቀሉ ወገኖች በጥሬ ገንዘብና በአይነት 20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ

96

ባህር ዳር፤ ታህሳስ 22 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል በአማራ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች በጥሬ ገንዘብና በአይነት 20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ።

ተቋማቱ ድጋፉን ለአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ዛሬ አስረክበዋል።

ከድጋፉ መካከል በአይነት 13 ሚሊዮን ብር ያበረከተው ኢንቨስትመንት ኮሚሽን  ሲሆን የኢትዮጰያ ኤሌክትሪክ ሃይል ደግሞ 4 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የአይነትና በጥሬ ገንዘብ 3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።

በተቋማቱ የተደረገው አይነት ድጋፍ የህፃናት አልሚ ምግብ፣ የምግብ ዘይና፣ አልባሳትን ያካተተ ነው።

የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዘላለም ልጃለም በርክክብ ስነ ስርአቱ ላይ እንዳሉት የሽብር በድኑ ወረራ ፈፅሞባቸው በነበሩ  አካባቢዎች በርካታ ዜጎች የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ይፈልጋሉ።

በሽብር ቡድኑ ወራራ 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዜጎች ተፈናቅለዋል፤ 9 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዜጎች ደግሞ ባሉበት ሆነው ለምግብ እህል እጥረት የተጋለጡ መሆናቸውን አመልክተዋል ።

የኢንቨስትመንት ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ተቋማት በዛሬው እለት ያደረጉት ድጋፍ የተፈናቀሉና ለችገር የተጋለጡ ወገኖችን ለመደገፍና ለማቋቋም ለሚደረገው ጥረት አስተዋጽኦ እንዳለው ገልፀዋል።

"ድጋፉ እርዳታ ለሚሹ ወገኖች በፍትሃዊነት እንዲደርስ ይደረጋል" ያሉት ኮሚሽነሩ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

በድጋፍ ርክክቡ የኢትዮጰያ ኤሌክትሪክ ሃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ፣ የኢትዮጰያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዳንኤል ተሬሳ ጨምሮ የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽነርና የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም