የሶማሊያ መሪዎች ወቅታዊ አለመግባባቶችን በሰላማዊ ውይይት እንዲፈቱ የአፍሪካ ህብረት አሳሰበ

106

ታህሳስ 22 ቀን 2014 (ኢዜአ) የሶማሊያ መሪዎች ወቅታዊ አለመግባባቶችን በሰላማዊ ውይይት እንዲፈቱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህመት አሳሰቡ።

የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህመት በወቅታዊ የሶማሊያ መሪዎች ፖለቲካዊ አለመግባባት ዙሪያ መግለጫ አውጥተዋል።

ሊቀመንበሩ በመግለጫቸው የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያን ፖለቲካዊ አለመረጋጋት በትኩረት እየተከታተለው ነው ብለዋል።

አክለውም የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሁሴን ሮብሌ በመካከላቸው ያለውን አለመግባባት በውይይት እንዲፈቱ አሳስበዋል።

መሪዎቹ ሀገሪቱን የባሰ አደጋ ላይ ከሚጥል እንቅስቃሴ እንዲቆጠቡም ነው ሙሳ ፋኪ ያስጠነቀቁት።

የአፍሪካ ህብረት በሶማሊያ ያለው የሰላም እጦት እና አለመረጋጋት እንዲፈታ በላቀ ሁኔታ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም