ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ያሉ ዳያስፖራዎች ያመጡትን የህክምና ግብዓት ድጋፍ አስረከቡ

64

ታህሳስ 22 ቀን 2014 (ኢዜአ) ለዳያስፖራው በቀረበው ጥሪ መሰረት ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ያሉ ዳያስፖራዎች ለጤና አገልግሎት እንዲውል ያመጡትን የህክምና ግብዓት ድጋፍ አስረከቡ።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ ማለዳ በቦሌ ዓለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው የህክምና ግብዓት ድጋፉን ተረክበዋል።

እናት አገራቸው ባደረገችው ጥሪ መሰረት ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ላይ የሚገኙ የዳያስፖራ አባላት የህክምና ግብዓትን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።

በተለይም ‘አንድ ሻንጣ ለወገኔ’ በሚል መሪ ሀሳብ ለጤና አገልግሎት ግብዓት የሚሆን ድጋፍ የማሰባሰብ ዘመቻ ዳያስፖራው ማካሄዱ ይታወሳል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ አንድ ሚሊዮን ዲያስፖራ ወደ ሀገር እንዲገባ ጥሪ ማድረጋቸውን ተከትሎ በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም