የሲዳማ ክልል ምክር ቤት አንደኛ መደበኛ ጉባኤ ነገ ይጀመራል

173

ሀዋሳ ታህሳስ 21/2014 (ኢዜአ) የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ስድስተኛ ዙር አንደኛ የሥራ ዘመን አንደኛ መደበኛ ጉባኤ ነገ እንደሚጀምር ተገለጸ።

የምክር ቤቱ  የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አዲሱ ዶራሞ ለኢዜአ እንደገለጹት ፤ ጉባኤው በሚኖረው የሁለት ቀናት ቆይታ የምክር ቤቱን ስድስተኛ ዙር መስራች ጉባኤ ቃለ ጉባኤ እንደሚያፀደቅ ይጠበቃል።

እንዲሁም  የክልሉን መንግስት የአስር ዓመት መሪ ዕቅድ ፣ የህግ አውጪ፣ህግ አስፈጻሚና ህግ ተርጓሚ የመንግስት አካላት የ2014 በጀት ዕቅድ ፣ የምክር ቤት የአባላት ሥነ-ምግባር ደንብ  ላይ ምከር ቤቱ ከሚወያይባቸው አጀንዳዎች መካከል ጠቅሰዋል።

ጉባዔው የተለያዩ   ሹመቶችን ተቀብሎ እንደሚያፀድቅ የሚጠበቅ መሆኑን ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልጸዋል።