የጋምቤላ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ክልላዊና ሀገራዊ ጉዳዩች ዙሪያ እየተወያዩ ነው

262

ታህሳስ 21 ቀን 2014 (ኢዜአ) የጋምቤላ ህዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ክልላዊና ሀገራዊ ጉዳዩች ዙሪያ እየተወያዩ ነው።

በጋምቤላ ከተማ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የተጀመረው የውይይቱ መድረክ ለአራት ቀናት በሚያደርገው ቆይታ ሀገሪቱ ተገዳ በገባችበት ጦርነት የተገኙ ሁለንተናዊ ድሎች ተጠብቀው ወደ ዘላቂ ሰላምና ልማት በሚሸጋገሩበት ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክር ተገልጿል።

‘በህልውና ጦርነቱ  ሂደት የተገኘው ሀገራዊ አንድነት፣ ተናቦና ተቀናጅቶ የመስራት ልምድ፣ በጋራ ዓላማ በጋራ የመስራት’ በሚሉ ሃሳቦች ዙሪያ ውይይት እንደሚደረግ ተጠቁሟል።

የአመራር ሁለንተናዊ ተሳትፎና ቁርጠኝነት ለሀገር ዘላቂ ብልጽግና የመምራት አስፈላጊነት ላይ  አመራሩ በጥልቀት እንደሚመክር ይጠበቃል።

የተገኘውን ድል ተከትሎ ሊመጡ የሚችሉ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የጸጥታ ፈተናዎችን በብቃት ማለፍና  በአግባቡ መምራት የሚለውም ሌላው የመድረኩ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑ ታውቋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼