ከኢትዮጵያ ውጡ በሚሉበት ወቅት ልጆቿ ግን ወደ እቅፍዋ በመትመም ታሪካዊ ጠላቶቻችንን አሳፍራቹሃል

84

ታህሳስ 20 ቀን 2014 (ኢዜአ) ከኢትዮጵያ ውጡ በሚሉበት ወቅት ልጆቿ ግን ወደ እቅፍዋ በመትመም ታሪካዊ ጠላቶቻችንን አሳፍራቹሃል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

የኢትዮጵያን ጥሪ ተቀብለው ወደ አገራቸው ለመጡ የዳያስፖራ አባላትም ምስጋና አቅርበዋል።

ወደ አገር ቤት ለመጡ ኢትዮጵያዊያንና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን ዲያስፖራዎች አዲስ አበባ ቤት ያፈራውን ሁሉ አሰናድታ እንደምታቀርብም ጠቁመዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ወዳጅነት አደባባይ ወደ አገር ቤት ለመጡ ኢትዮጵያዊያንና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ከኢትዮጵያ ውጡ በሚባልበት ወቅት ልጆቿ ግን ወደ እቅፍዋ በመትመም ታሪካዊ ጠላቶቻችንን አሳፍራቹሃልና ምስጋና ይገባቹሃል ብለዋል፡፡

የውስጥና የውጭ ጠላቶች አንድ ላይ አብረው ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማበርታት ሲታትሩ ‘ኖ ሞር’ ብላችሁ በአለም አደባባይ እውነታውን የመሰከራቹ ጀግኖች ናችሁ በድጋሚ ኢትዮጰያ ታመሰግናቹሃለች ብለዋል፡፡

በመሆኑም የእናት አገራችሁ መዲና አዲስ አበባ ቤት ያፈራውን አዘጋጅታ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ትቀበላቹሃለች ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም