የዳያስፖራዎች የአቀባባል ስነ ስርዓት በወዳጅነት አደባባይ እየተካሄደ ነው

160

ታህሳስ 20 ቀን 2014 (ኢዜአ) የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ “የአንድ ሚሊዮን ዳያስፖራ የአገር ቤት ጉዞ ጥሪ” ተቀብለው ለመጡ ዳያስፖራዎች የአቀባባል ስነ ስርዓት በወዳጅነት አደባባይ እየተካሄደ ነው።

በስነ ስርዓቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤና ሌሎች የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

May be an image of 9 people, people standing and outdoors

የመርሃ ግብሩ ታዳሚዎች በወዳጅነት አደባባይ ለዳያስፖራዎቹ የአገር ቤት ጥሪ የተዘጋጀውን አውደ ርዕይ ጎብኝተዋል።

በውጭ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ አገር ቤት እንዲመጡ የቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው በርካታ ዳያስፖራዎች ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ መሆኑ ይታወቃል።