በዓሉ የመደጋገፍ ባህላችንን ያሳየንበት ነው

95

ሐረር፣ ታህሳስ 19 ቀን 2014 (ኢዜአ) በዓሉ ሰላማችንን እና የመደጋገፍ ባህላችንን ይበልጥ ለሌሎች ያሳየንበት ነው ሲሉ በቁልቢ ገብርኤል በዓለ ንግስ ላይ የታደሙ የእምነቱ ተከታዮች ተናገሩ።

ዛሬ የተከበረው ዓመታዊው የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓል ታዳሚዎች ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት እንደገለጹት፤ ለሀገሪቱ ሰላም መጎልበት በጸሎት መትጋት ያስፈልጋል።

በበዓሉ ጉዞ እና በገዳሙ ስፍራ የነበረው የሰላም ሁኔታ እንዳስደሰታቸው የገለጹት አስተያየት ሰጪዎቹ፤ የአካባቢው ማህበረሰብም ለምዕመናኑ ያደረጉት አቀባበል እጅግ አስደናቂ መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይ ወጣቱ የአካባቢን ሰላም በመጠበቅ፣ አቅመ ደካሞችንና የተጎዱ ዜጎችን የመደገፉን ስራ ማጠናከር እንዳለበት አስገንዝበዋል።

በዓሉ በመንገድም ሆነ በገዳሙ ቆይታቸው አስደሳች እና ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ መከበሩም እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል።

በዓሉ ሰላም ሆኖ ሊጠናቀቅ የቻለው የበዓሉ ታዳሚዎችና የጸጥታ አካላት የድርሻቸውን በአግባቡ መወጣት በመቻላቸው እንደሆነም ገልጸዋል።

በዓሉ በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ ቀን ከሌሊት ሲሰሩ ለነበሩ የጸጥታ ሃይሎች ምስጋና አቅርበዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም