የአኝዋ ብሄረሰብ ዞን ለተፈናቃይ ወገኖች ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ

177

ሰመራ፣ ታህሳስ 19 ቀን 2014 (ኢዜአ) በጋምቤላ ክልል የአኝዋ ብሄረሰብ ዞን በአፋር ክልል አሸባሪው ህወሓት በፈጸመው ወረራ ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የምግብና የአልባሳት ድጋፍ አደረገ።

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ድጋፉን ከአኝዋ ብሄረሰብ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ኡጁሉ ንጎ ዛሬ በሰመራ ከተማ ተረክበዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ አወል የዞኑ ሕዝብ ለተፈናቃዮቹ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው፤ ዜጎች በጦርነቱ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍ እያደረጉት ያለውን ርብርብ አድንቀዋል።

ኢትዮጵያውያን ያሳዩት አንድነትና ህብረት ለተጎጂዎች ሰብዓዊ ድጋፍ ከማድረስ ባለፈ ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ ገልጸዋል።


ሁሉም ክልሎች ያደረጉት እገዛና ወገናዊ አጋርነት የመረዳዳት እሴቶችን ያጠናክራል ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።

የአኝዋ ብሄረሰብ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ኡጁሉ ንጎ በበኩላቸው፤ የዞኑ ሕዝብ ለተፈናቀሉ ወገኖቹ ያለው አጋርነት ለመግለጽ ድጋፉን ማድረጉን አስታውቀዋል።

ድጋፉ ተፈናቃዮቹ መልሰው እስኪቋቋሙ ድረስ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼