የሰላም ሚኒስቴር ብሄራዊ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስልጠና ማስጀመሪያ መርሃ ግብር እያካሄደ ነው

362


ሆሳዕና ፤ ታህሳስ 19/2014 (ኢዜአ) የሰላም ሚኒስቴር ሶስተኛ ዙር ብሄራዊ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስልጠና ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ እያካሄደ ነው።


በመርሐ ግብሩ ላይ የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዱዓለም፣ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችና መምህራን ተገኝተዋል።


በዚህኛው ዙር ከ2 ሺህ 200 በላይ ተማሪዎችን በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለማስልጠን ዝግጅት መጠናቀቁ ተገልጿል።


መርሐ ግብሩ ወጣቶችን የሰላምና የልማት ባለቤት የማድረግ ዓላማ እንዳለውም ተነግሯል።

አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የስልጠናው ተሳታፊዎች፤ በቆይታቸው የሚያገኙትን ዕውቀትና ልምድ በመጠቀም በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንደሚሰጡ የተናገሩት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም