የአዲስ አበባ ክፍለ ከተማ ምክር ቤቶች አዳዲስ ዋና ስራ አስፈፃሚዎችን ሾሙ

99
አዲስ አበባ ነሀሴ 20/2010 የአዲስ አበባ ክፍለ ከተማ ምክር ቤቶች አዳዲስ ዋና ስራ አስፈፃሚዎችን ሾሙ። በአዲስ አበባ የሚገኙት 10 ክፍለ ከተሞች ምክር ቤቶች ዛሬ አስቸኳይ ጉባኤዎቻቸውን አካሂደው ሹመቱን ማጽደቃቸውን የከተማው አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል። በዚህም መሰረት፦ በአራዳ ክፍለ ከተማ፦ ወይዘሮ  አበባ እሸቴ ዋና ስራ አስፈፃሚ እና ወይዘሮ ህይወት ጉግሳ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ በልደታ ክፍለ ከተማ፦ አቶ አለማው ማሙዬ ዋና ስራ አስፈፃሚ እና  ወይዘሮ  ሁሉአገርሽ ተፈራ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ፦ አቶ የትናዬት ሙሉጌታ ዋና ስራ አስፈፃሚ እና ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ በጉለሌ ክፍለ ከተማ፦ አቶ ፍስሃዬ ክፍሌ ዋና ስራ አስፈፃሚ እና አቶ አሸናፊ ደጀኔ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ በኮልፌ ክፍለ ከተማ፦አቶ ኢሳያስ ምህረት ዋና ስራ አስፈፃሚ እና አቶ ቴዎድሮስ ከበደ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ በየካ ክፍለ ከተማ፦ ወይዘሮ ዓለምፀሃይ ጳውሎስ ዋና ስራ አስፈፃሚ እና አቶ ወንድዬ ደረጀ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ በአቃቂ ክፍለ ከተማ፦ ወይዘሮ አስራት ተሰማ ዋና ስራ አስፈፃሚ እና አቶ አስገዶም አረቄ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ በቦሌ ክፍለ ከተማ፦ አቶ ጥላሁን ፈቃዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ እና አቶ በየነ ፍስሃ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፦ አቶ ኃይሉ ታደሰ ዋና ስራ አስፈፃሚ እና አቶ ዮሐንስ በርሄ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ፦ አቶ ኤፍሬም አድማሱ ዋና ስራ አስፈፃሚ እና አቶ ሙባረክ ከማል ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ በመሆን ተሹመዋል፡፡    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም