ዶክተር ጥላሁን ጎሹና አጋሮቻቸው 4 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ የጤና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ

151

ታህሳስ 17 ቀን 2014 (ኢዜአ) በአሜሪካ የሚኖሩት ዶክተር ጥላሁን ጎሹና አጋሮቻቸው አሸባሪው ሕወሓት በሰሜን ኢትዮጵያ ላወደማቸውና ለዘረፋቸው የጤና ተቋማት ድጋፍ የሚውል 4 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ የጤና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።

ዶክተር ጥላሁን በሚሰሩበት ‘ምህረት ሜዲካል ሰፕላይ ግሩፕ ‘ ከአጋሮቻቸው ጋር በመሆን የማጓጓዣ ወጪውን ጨምሮ 4 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ የሕክምና ቁሳቁሶች፣ የሕክምና መሳሪያዎች፣ ቪታሚኖችና አንድ ኮንቴነር ሙሉ መድሐኒቶችን በመርከብ ወደ ኢትዮጵያ አጓጉዘዋል።

ዶክተር ጥላሁን ጎሹና አጋሮቻቸው ስላደረጉት ድጋፍ መረጃውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ያጋሩት በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፍጹም አረጋ ምስጋና አቅርበዋል።