አሜሪካ አጎዋን በኢትዮጵያ ላይ የንግድ ጦር መሳርያ አድርጋ እየተጠቀመችው ነው - ላውረንስ ፍሪማን

90

ታህሳስ 16 ቀን 2014 (ኢዜአ) አሜሪካ ኢትዮጵያን ከአጎዋ ንግድ ስርዓት በማስወጣት አጎዋን የንግድ ጦር መሳርያ አድርጋ እየተጠቀመችው ነው ሲሉ ላውረንስ ፍሪማን አመለከቱ።

በአፍሪካ የፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ ከ30 ዓመታት በላይ ምርምር ያደረጉት ላውረንስ ፍሪማን የባይደን አስተዳደር ኢትዮጵያን ከአጎዋ የንግድ ስርዓት መሰረዙን ተከትሎ “ምን አይነት የግብዝነት ውሳኔ ነው” ሲሉ ተችተዋል።

በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደርና የኢኮኖሚ ጉዳትን የሚጨምር ውሳኔ ነው ሲሉም ነው ውሳኔውን የተቹት።

ውሳኔው የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ባለው ቅራኔ የተወሰነ መሆኑን አመልክተው፤ "የኔን አሜሪካ አይወክልም" ብለዋል።

“ይህ ውሳኔ አሜሪካ አጎዋን በኢትዮጵያ ላይ የንግድ ጦር መሳርያ አድርጋ እየተጠቀመችው ለመሆኑም ማሳያ ነው” ሲሉ በትዊተር ገጻቸው አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም