የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥምረት ዓመታዊ ጉባዔ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተጀመረ

169

ሐረር ፤ ታህሳስ 14 ቀን 2014(ኢዜአ) በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች ጥምረት ዓመታዊ ጉባዔ ዛሬ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተጀመረ።

የጥምረቱ ጉባዔ በጥናትና ምርምር፣በማማከር አገልግሎት፣በአቅም ግንባታ ስልጠና እና በሌሎች ዘርፎች እያከናወኑ የሚገኙ ስራዎች ላይ እንደሚመክር ይጠበቃል።

ዓላማውም በዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች መካከል የእርስ በርስ ግንኙነት እና ትስስርን በማጎልበት ለመንግስት የልማት ስራዎች መሳካት የሚያደርጉትን ድጋፍ ለማጠናከር እንደሆነ ተገልጿል።

በጉባዔው ላይ በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሌላ  የድሬዳዋ ፣ጅግጅጋ ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እና የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲዎች በተጋባዥነት እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡