ኢትዮጵያን ከአጎዋ የማገድ ውሳኔ ሚዛናዊ ያልሆነና የአሜሪካ ባለሃብቶችን እንቅስቃሴ የሚጎዳ በመሆኑ በድጋሚ ሊታይ ይገባል

81

ታህሳስ 14 ቀን 2014 (ኢዜአ) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ኢትዮጵያን ከአጎዋ የማገድ ውሳኔ ሚዛናዊ ያልሆነና የአሜሪካ ባለሃብቶችን የሚጎዳ በመሆኑ ውሳኔው በድጋሚ እንዲታይ በካሊፎርኒያ ዴሞክራቲክ ፓርቲን የወከሉት የኮንግረስ አባሏ ካረን ባስ እና ሴናተሩ ክሪስ ቫን ሆለን ጠየቁ።

ፕሬዚዳንቱ ውሳኔውን መልሰው እንዲያጤኑት በጋራ በጻፉት ደብዳቤ ጠይቀዋል።

አሜሪካ ለአፍሪካ አገሮች ከሰጠችው የቀረጥ ነፃ እድል (አጎዋ) ማዕቀፍ ኢትዮጵያን ለማገድ ውሳኔ ማሳለፏ ይታወሳል።

ውሳኔው ተገቢ ያልሆነ ሚዛናዊነት የሌለውና የአሜሪካን ባለሃብቶች ጭምር ሊጎዳ እንደሚችል ካረን ባስ እና ክሪስ ቫን አመላክተዋል።

ውሳኔው በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል ባለው ግጭት ውስጥ ምንም አይነት አስተዋጽኦ የሌላቸው ንጹሃንን የሚጎዳና አፍራሽ ውጤት የሚያስከትል በመሆኑ አጥብቀን ተቃውመነዋል ብለዋል።

ህጻናትና ሴቶችን ለድህነት የሚያጋልጥ፣ ኢትዮጵያውያን ለብዙ አመታት ሰርተው ያመጡትን የኢኮኖሚ መሻሻል የሚጎዳ የአሜሪካውያን ባለሃብቶች ላይም ጫና የሚኖረው መሆኑን አመላክተዋል።

የባይደን አስተዳደር የጉዳዩን ክብደት በማየት ተጨማሪ ጊዜ በመስጠት ኢትዮጵያ ማእቀፉ ውስጥ እንድትቆይ እንዲያደርግ አሳስበዋል።

ግጭቱ በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ እንዲያገኝ የበኩላቸውን እንደሚያደርጉም ገልጸዋል።

_ አካባቢህን ጠብቅ፣ _

ወደ ግንባር ዝመት፣_

መከላከያን ደግፍ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም