አሸባሪው ህወሃት በቆቦ ከተማ በቃላት የማይገለጽ ግፍና ጭካኔ ፈጽሟል

228

ታህሳስ 12 ቀን 2014 (ኢዜአ) አሸባሪው ህወሃት በቆቦ ከተማ በቃላት የማይገለጽ ግፍና ጭካኔ ፈጽሟል ሲሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ 

የሽብር ቡድኑ ወራሪ ኃይሎች በቆቦ ከተማ በቆዩባቸው ጊዜያት በነዋሪዎች ላይ እጅግ አሰቃቂ ግፍ የፈጸሙ ሲሆን፤ በተለይ ወጣቶችን በጅምላ ጨፍጭፈዋል፤ በርካታ ሴቶችን ደግሞ አስገድደው ደፍረዋል፡፡

ኢዜአ በከተማዋ ተገኝቶ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እንደሚሉት፤ የአሸባሪ ቡድኑ ወራሪ ኃይሎች ቤት ለቤት እየገቡ ሰላማዊ ዜጎችን ገድለዋል፤ የሚችሉትን ያህል ሃብት ዘርፈዋል፡፡

በአንድ ቀን ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎች መገደላቸውን ጠቅሰው፤ አሸባሪ ቡድኑ ከተማዋን ወደ ኋላ እንድትመለስ አድርጎ አውድሟታልም ነው ያሉት፡፡

አሸባሪ ቡድኑ በከተማዋ የሚኖሩ የአእምሮ ህመምተኞችን ጭምር መግደሉን ጠቅሰው፤ የሽብር ቡድኑ ቤት ለቤት በመግባት ሽሮና በርበሬ እስከመዝረፍ የደረሰ ነውረኝነት መፈጸሙን አንስተዋል፡፡

የሰላም አየር መተንፈስ የጀመርነው አሁን ነው የሚሉት አስተያየት ሰጭዎቹ ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዞ ከተማዋን ወደ ልማት ለመመለስ እንዲሰራም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

_ አካባቢህን ጠብቅ፣

_ ወደ ግንባር ዝመት፣

_ መከላከያን ደግፍ።