የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደ አገር ቤት ለሚገቡ ዳያስፖራዎች የተቀላጠፈ የውጭ ምንዛሬ አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅቷል

160

ታህሳስ 12 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደ አገር ቤት ለሚገቡ ዳያስፖራዎች የተቀላጠፈ የውጭ ምንዛሬ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን አስታወቀ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ አንድ ሚሊዮን ዳያስፖራ ወደ አገር ቤት በሚል ባደረጉት ጥሪ መሰረት ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ አገር ቤት በመግባት ላይ ይገኛሉ።

በዚሁ መሰረት ወደ አገር ቤት ለሚገቡ እንግዶች ፈጣንና ቀልጣፋ የውጭ ምንዛሬ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን የኢትዮጵያን ንግድ ባንክ  አስታውቋል።

የባንኩ የማእከላዊ ሪጅን ምክትል ፕሬዚዳንት ኪዳኔ መንገሻ ወደ አገር ቤት የሚገቡ እንግዶች ቀልጣፋ የምንዛሬ አገልግሎት እንዲያገኙ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።

የውጭ ምንዛሬ አማራጮችን በማስፋት የቪዛ ካርድ፣ የዩኒየን ፔይ እና የማስተር ካርድ የሚመነዝሩ ከ3 ሺህ በላይ ኤቲኤሞችና የፎሬክስ ኤቲኤሞች መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ23 ኛው ዙር የ”ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” መርሃ ግብር እጣ አሸናፊ እድለኞችን ሸልሟል።

በዛሬው ይቆጥቡ  ይመንዝሩ ይሸለሙ ፕሮግራም አንድ የቤት አውቶሞቢል፣ ሁለት ባጃጅና 20 ላፕቶፖችና ለሌችም ሽልማቶች ለእድለኞች ወጥተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ”ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” መርሃ ግብር ከጀመረ እስካሁን በድምሩ ከ52 ቢሊዮን ብር በላይ ለባለ እድለኞች መሸለሙ ታውቋል።

የወጭ ንግድን በማሳለጥና አዳዲስ አሰራሮችን በመዘርጋት ባለፈው በጀት አመት 2 ነጥብ 64 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱ ይታወቃል።

_ አካባቢህን ጠብቅ፣

_ ወደ ግንባር ዝመት፣

_ መከላከያን ደግፍ።