የተመድ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ላይ ያቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ 15 አገራት ተቃወሙ

256

ታህሳስ 08 ቀን 2014 (ኢዜአ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ላይ ያቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ 15 አገራት ተቃወሙ።

ምክር ቤቱ ያቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ከተቃወሙት 15 አገሮች በተጨማሪ 11 አገሮች ድምጸ ተዓቅቦ አድርገዋል።

ኤርትራ፣ ሕንድ፣ ጋቦን፣ ቡርኪናፋሶ፣ ቻይና፣ ናምቢያ፣ ቬንዙዌላ፣ ኩባ፣ ፓኪስታን፣ ፊሊፒንስ፣ ሶማሊያ፣ ሩሲያ፣ ካሜሮን፣ ኮትዲቭዋርና ቦሊቪያ ረቂቅ የውሳኔ ሃሳቡን የተቃወሙ አገራት ናቸው።

በረቂቅ የውሳኔ ሀሳቡ ላይ ድምጸ ተዓቅቦ ያደረጉ 11 አገራት ደግሞ ሊቢያ፣ ማላዊ፣ ሱዳን፣ ሴኔጋል፣ ቶጎ፣ ሞሪታኒያ፣ ባህሬን፣ ባንግላዴሽ፣ ኔፓል፣ ኡዝቤኪስታንና ኢንዶኔዢያ ናቸው።

ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ላይ የጠራውን ልዩ ስብሰባ 13 የአፍሪካ አገራትን ጨምሮ 22 የምክር ቤቱ አባል አገራት እንደተቃወሙት ይታወቃል።

_ አካባቢህን ጠብቅ፣

_ ወደ ግንባር ዝመት፣

_ መከላከያን ደግፍ።