22 አገራት የተመድ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ስብስባውን በመቃወም ከኢትዮጵያ ጎን ቆመዋል

230

ታህሳስ 08 ቀን 2014 (ኢዜአ) 13 የአፍሪካ አገራትን ጨምሮ 22 አገራት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ላይ የጠራውን ልዩ ስብሰባ በመቃወም ከኢትዮጵያ ጎን ተሰልፈዋል።

ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ላይ የጠራው ስብስባ ተካሂዷል።

ካሜሮን ተወካይ 13ቱ የምክር ቤቱ አባላት ወክለው ባደረጉት ንግግር አገራቱ በኢትዮጵያ ላይ የተጠራውን ስብሰባና የቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ እንደሚቃወሙት ገልጸዋል።

ቡርኪናፋሶ፣ ቶጎ፣ ኮትዲቭዋር፣ ማላዊ፣ ሞሪታኒያ፣ ጋቦን፣ ሊቢያ፣ ናምቢያ፣ ሴኔጋል፣ ሱዳን፣ ካሜሮን፣ ሶማሊያና ኤርትራ የተመድ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት የአፍሪካ አባል አገራት ናቸው።

የምክር ቤቱ ልዩ ስብሰባ በኢትዮጵያ ዙሪያ እንዲሰበሰብ ጥሪ ካደረጉት አገራት መካከል የአፍሪካ አገራት እንደሌሉበት ይታወሳል።

ከአፍሪካ አገራት በተጨማሪ የምክር ቤቱ አባል የሆኑት ቻይናና ሩሲያ የተጠራውን ስብስባ የተቃወሙ ሲሆን ኢትዮጵያ ያለማንም ጣልቃ ገብነት የሯሷን ችግር በራሷ መፍታት እንደምትችል ገልጸዋል።

የምክር ቤቱ አባል የሆኑት ኩባ፣ ሕንድ፣ ሩሲያ፣ ኢንዶኔዢያ፣ ቬንዙዌላ፣ ፊሊፒንስ፣ ፓኪስታንና ቦሊቪያ በተመሳሳይ የተጠራውን ስብሰባ ተቃውመው ኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ በራሷ መፍታት እንደምትችል ገልጸዋል።

የተመድ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት 37 ታዛቢ አገራት መካከል ኢራን፣ ስሪላንካና ናይጄሪያ የኢትዮጵያን ጉዳይ ለኢትዮጵያ መተው እንደሚገባ ተናግረዋል።

በጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ዘነበ ከበደ በኢትዮጵያ ላይ የተጠራው ልዩ ስብሰባ ስብሰባ የሚያሳልፋቸውን ማናቸውንም ውሳኔዎች እንደማትቀበልና እንደማትተገብር በስብስባ ላይ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል።

ልዩ ስብሰባ የተመድ የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቢሮና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ያደረጉትን የጋራ ምርመራ የናቀ መሆኑን አመልክተዋል።

የምክር ቤቱ አባላት በስብሰባው ላይ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ እንዲቃወሙና ውድቅ እንዲያደርጉ አምባሳደር ዘነበ ጠይቀዋል።

ምክር ቤቱ አሸባሪው ሕወሃት በአማራና አፋር ክልሎች የተፈጸሙ ድርጊቶች ላይ ምርመራ ለማድረግ ፍላጎት አለማሳየቱና የፖለቲካ ጫና ለማሳደር እንደ መሳሪያነት መዋሉ የሚያሳዝን መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በታሪክ የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ሊጭኑባት የፈለጉ ሃይሎችን ብቻዋን በዓለም መድረክ በመታገል አሸንፋለች አሁንም ከአጋሮቿ ጋር በመሆን ትግሏን ትቀጥላለች ብለዋል።

_ አካባቢህን ጠብቅ፣

_ ወደ ግንባር ዝመት፣

_ መከላከያን ደግፍ።