አሸባሪው የህወሃት ቡድን በሴቶችና ህፃናት ላይ የፈጸመውን ጭፍጨፋና አስገድዶ መድፈር የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በሰመራ ከተማ ተካሄደ

61

 ታህሳስ 08/2014(ኢዜአ) አሸባሪው የህወሃት ቡድን በሴቶችና ህፃናት ላይ የፈጸመውን ጭካኔ የተሞላበት ጭፍጨፋና አስገድዶ መድፈር የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በአፋር ክልል ርዕሰ መዲና ሰመራ ተካሄደ ።

ሰልፉን ያካሄዱት የሰመራ፣ ሎጊያ እና ዱብቲ ነዋሪዎች በጋራ በመሆን  ሲሆን፤ የሰልፉ ተሳታፊዎች ከአሸባሪ ቡድኑ በተጨማሪ በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን የውጭ ጣልቃገብነት አውግዘዋል፡፡

በሰልፉ "እኛ የአድዋ ጀግኖች ልጆች ነን አገራችን አናስደፍርም" "ፆታ ተኮር ጥቃት አሁኑኑ ይቁም"፤ "በአፋርና አማራ ክልል የተፈጸመው ጥቃትና የጅምላ ጭፍጨፋ ፍትህ ያግኝ"፤ "ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃንና ሰብዓዊ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ላይ የሚሰራጩት የተዛባ መረጃ ይቁም" የሚሉና ሌሎች መልዕክቶች ተላልፈዋል፡፡

የሰላማዊ ሰልፉ ዓላማ አሸባሪው ህወሃት ቡድን በአፋርና አማራ ክልሎች በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች በሴቶች፣ ህፃናት እና አረጋዊያን  ላይ የፈጸመው ጭፍጨፋ፣ አስገድዶ መድፈር እና ሌሎች ፆታዊ ጥቃቶችን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማሳወቅ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም