ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ አቢጃን ከተማ ገቡ

134

ታህሳስ 7/2014 (ኢዜአ)ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ለመወያየት ኮትዲቯር አቢጃን ከተማ ገብተዋል።

በቆይታቸው ከኮቲዲቯር ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ በሚጠናከርበት ሁኔታ ከሀገሪቱ ፕሬዝደንት አላሳን ኦታራ ጋር ይወያያሉ።

ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ በተጨማሪም ከኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ እና ከአፍሪካ ልማት ባንክ መሪዎች ጋር እንደሚወያዩ ከፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።