የቬትናም ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች እንዲሳተፉ ፍላጎት አለ-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

58
አዲስ አበባ ነሀሴ 18/2010 የቬትናም ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች  እንዲሳተፉ ፍላጎት እንዳለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ይሕ የተለገለፀው ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ የቬትናም የንግዱ ማሕበረሰብ የልዑካን ቡድን አባላት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ከኢትዮጵያ አቻቸው ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በዚሁ ወቅት እንዳሉት የቬትናም ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋእለ ንዋያቸውን ቢያፈሱ ውጤታማ አንደሚሆኑ ገልፀዋል። ኢትዮጵያ የሚስብና አዋጭ የሆነ የኢንቨስትመንት አማራጭ ያላት ሲሆን በመንግስት የሚደረገውም ማበረታቻ ተጠቃሚ የሚያደርጋቸው መሆኑንም ተናግረዋል። እነዚሁ ባለሃብቶች በተለይ በጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ፣ በቆዳ ውጤቶች፣ በታዳሽ ኢንርጂ፣ በኮንስትራሽንና በአግሮ ፕሮሰሲንግ መስኮች ያሉት ማበረታቻዎች ስኬታማ እንደሚያደርጋቸው አስረድተዋል። በተጨማሪም የአገሪቱ ባለሃብቶችና ኢንተርፕራይዞች በትላልቅ እርሻዎች መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን ለዚህም አመቺ የአየር ሁኔታ እንዲሁም በቂ የሆነ መሬትና የሰው ኃይል እንዳለም በመጠቆም። ኢትዮጵያ ካሏት በርካታ እምቅ ሃብት ውስጥ የእንስሳት ሃብቷ ከአፍሪካ አንደኛ እንደሆነ የገለጹት ሚኒሰትር ዴኤታው ይሕም የቆዳ ውጤቶችን ለማምረት  ሰፊና ምቹ እድልን እንደሚሰጥም በገለጻው ላይ አንስተዋል። የቬትናም  የእቅድና ኢንቨስትመንት ሚንስትር ሙጉዩን ቺሊ ዱንግ በበኩላቸው  የቬትናም ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የኢንቨስትመንት አማራጭ በመጠቀም በጋራ መስራት ይፈልጋሉ። ከዚህ ውስጥም በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፣ በቴሌኮሙኒኬሽን ፣ በማእድን፣ በኢነርጂ፣ በተለያዩ ኬሚካል አቅርቦትና የኮንስትራክሽን ዘርፉ ተጠቃሽ ነው። በዛሬው እለት  ሃምሳ የሚደርሱ የንግዱ ማሕበረሰብ አባላት ከልዑካን ቡድኑ ጋር የመጡ ሲሆን ያሉትን ማበረታቻዎች ተጠቅመው የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚፈልጉም ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም