አሸባሪው ህወሃትና ተላላኪዎቹ የሚፈጽሙትን የንጹሃን ጭፍጨፋና ጥቃት የሚቃወም ሰልፍ በጋምቤላ እየተካሄደ ነው

89

ጋምቤላ፤ ታህሳስ 7/2014(ኢዜአ) አሸባሪው ህወሃትና የጥፋት ተላላኪዎቹ ህጻናትን ጨምሮ በሴቶች ላይ የሚፈጽሙትን ፆታዊ ጥቃትና የንጹሃን ጭፍጨፋ የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በጋምቤላ ከተማ እየተካሄደ ነው።

አሸባሪው ህወሃት በአማራና አፋር ክልሎች ሴቶችን በመድፈርና ንጹሃን ዜጎችን በግፍ በመጨፍጨፍ በፈጸመው አስከፊ ወንጀል በአለም አቀፍ ህግ ሊጠየቅ ይገባል፤ ምዕራባዊያን ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉት ጫና ያቁሙ የሚሉ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።

አሜሪካን ጨምሮ የአንዳንድ ምዕራባዊያን መገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያን እውነት በመደበቅ እያሰራጩት ያለውን የሀሰት ዘገባ በመቃወም ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ጠይቀዋል።

ሰልፈኞቹ በከተማው በመዘዋወር ድምጻቸውን ካሰሙ በኋላ በጋምቤላ ስታዲየም ተሰባስበው መልዕክቶችን እያስተላለፉ ይገኛሉ፡፡

በሰልፉ ላይ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስን ጨምሮ የጋምቤላ ክልል የሴቶች አደረጃጀቶችና ሴት ተማሪዎች እየተሳተፉ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም