የክላሽንኮቭ ጥይት ደብቃ የተገኘች ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች

95

ደብረ ታቦር ታህሳስ 06/2014 በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረ ታቦር ከተማ የክላሽንኮቨ ጥይት ደብቃ የተገኘች ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሏን ፖሊስ አስታወቀ።

የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢኒስፔክተር ያለው ዘለቀ ለኢዜአ እንደገለጹት ግለሰቧ በቁጥጥር ስር የዋለችው ትናንት ምሽት ሶስት ሰዓት ላይ ነው።

ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት በከተማው ቀበሌ 02 በሚገኝ መኖሪያ ቤቷ  ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ የክላሽንኮቭ ጠብመንጃ ጥይት መገኘቱን ተናግረዋል ።

ተጠርጣሪ ግለሰቧ በቁጥጥር ስር ውላ ምርመራ እየተደረገባት መሆኑን ጠቁመዋል ።

ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ለመያዝም ክትትል እየተደረገ መሆኑን ዋና ኢንስፔክተሩ አስታውቀዋል።

ህብረተሰቡ አካባቢውን  ከህገ ወጥ ተግባራትና ሰርጎ ገቦች ለመጠበቅ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም