የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ እያካሄደ ነው

202

ድሬዳዋ ፣ታህሳስ 5/2014 (ኢዜአ) የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የአንደኛ አመት 7ኛ አስቸኳይ ጉባኤ እየተካሄደ ነው።

አስቸኳይ ጉባኤው የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ፕላን ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ ፣የአስተዳደሩን መዋቅራዊ ፕላን ማፅደቂያ ፣የድሬደዋ አስተዳደር አስፈፃሚና ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላትን እንደገና ለማቋቋምና ተግባርና ኃላፊነታቸውን ለመወሰን በወጡ ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል ።

በተጨማሪም የተለያዩ ሹመቶችን  እንደሚሰጥ ከመርሀ ግብሩ ለማወቅ ተችሏል።

የምክር ቤቱ አባላት አሜሪካንን ጨምሮ አንዳንድ የምዕራባውያን አገራትና  መገናኛ ብዙሀኖቻቸው በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነትና ጫና እንዲያቆሙ የተጀመረውን “ይበቃል ” ዘመቻ በግንባር ቀደምነት መቀላቀላቸውን  አሳውቀዋል ።