የ’በቃ' ዘመቻ አካል የሆነ ሰልፍ በአውስትራሊያ ሜልቦርን ተካሄደ

81

ታህሳስ 03 ቀን 2014 (ኢዜአ) የ’በቃ' ወይም '#NoMore' ዘመቻ አካል የሆነ ሰላማዊ ሰልፍ በአውስትራሊያ ሜልቦርን ከተማ በአውስትራሊያ ፓርላማ ፊት ለፊት ተካሄደ።

ሰልፈኞቹ ባሰሙት መፈክር የምዕራቡ ዓለም አንዳንድ አገራት በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉት ያለውን ያልተገባ ጫናና ጣልቃ ገብነት አውግዘዋል።

የምዕራባውያኑ መገናኛ ብዙሃኖች በኢትዮጵያ ላይ የሚያሰራጯቸውን ሀሰተኛ ዘገባዎችን እንዲያቆሙና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አሸባሪው ሕወሓት በአማራና አፋር ክልሎች የፈጸማቸውን በደሎች እንዲያወግዙ ጠይቀዋል።

አሸባሪው የሕወሓት ቡድን ድርጊቶች በዓለም አቀፍ ወንጀል የሚያስጠይቅ እንደሆም አስገንዝበዋል።

'ኢትዮጵያ አትፈርስም፣ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች፣ ከኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት ጎን ነን፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሕዝብ ድምጽ የተመረጠውን መንግስት ማክበርና እውቅና መስጠት አለበት' የሚሉና ሌሎች 'የበቃ' እንቅስቃሴ መልዕክቶች በሰልፉ ላይ ተላልፈዋል።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በአውስትራሊያ የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ አባላትና የኢትዮጵያ ወዳጆች መሳተፋቸውን ኤዜአ ከሰልፉ አዘጋጆች ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ሰልፉን ያዘጋጁት በአውስትራሊያ የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ አባላት መሆናቸው ተገልጿል።

'የበቃ' ወይም '#NoMore' ዘመቻ አካል የሆኑ ሰላማዊ ሰልፎች ዛሬ በዴንማርክ ኮፐንሀገንና በግሪክ አቴንስ ይካሄዳሉ።

'የበቃ' ወይም #NoMore እንቅስቃሴ አፍሪካ፣ አውሮፓ፣ እስያ፣ ሰሜን አሜሪካና ኦሺኒያ አህጉራትን አዳርሷል።

_ አካባቢህን ጠብቅ፣

_ ወደ ግንባር ዝመት፣

_ መከላከያን ደግፍ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም