የአማራ ባለሃብቶች ጥምረት ለአገሩ ህልውና ከልጁ ጋር በክብር ለተሰዋው አቶ እሸቴ ሞገስ ቤተሰቦች 2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

169

ታህሳስ 02 ቀን 2014 (ኢዜአ) የአማራ ባለሃብቶች ጥምረት ለአገሩ ህልውና ከልጁ ጋር በክብር ለተሰዋው አቶ እሸቴ ሞገስ ቤተሰቦች 2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።

የተደረገውን ድጋፍ የባለሃብቶቹ ጥምረት ተወካይ አቶ ዮናስ መኮንን ለአቶ እሸቴ ሞገስ ታናሽ ወንድም ዶክተር ይተብቱ ሞገስ ተረክበዋል፡፡

አቶ እሸቴ ሞገስ  ከልጃቸው ይታገስ እሸቴ ጋር በመሆን በሸዋሮቢት ሳላይሽ ላይ ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ ብሎ የተነሳውን የአሸባሪው ህወሃት ዘጠኝ ወራሪ ኃይሎችን በጀግንነት በመግደል በክብር መሰዋታቸው ይታወሳል፡፡

_ አካባቢህን ጠብቅ፣

_ ወደ ግንባር ዝመት፣

_ መከላከያን ደግፍ።