የኢንዱስትሪዎችን ምርትና ምርታማነት ማሳደግ በዘርፉ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢንዱስትሪዎችን ምርትና ምርታማነት ማሳደግ በዘርፉ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው
207
ታህሳስ 02 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢንዱስትሪዎችን ምርትና ምርታማነት ማሳደግ በዘርፉ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ተናገሩ፡፡
በሞጆ ከተማ የሚገኙ የቆዳ ኢንዱስትሪዎችን የጎበኙት አቶ መላኩ አለበል በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማሩ የግል ሴክተሮችን በቅርበት መደገፍ እና ማበረታት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
በአገሪቷ ከሚገኙ 27 ያህል መካከለኛ እና ከፍተኛ የቆዳ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ 19 የሚሆኑት የተሻለ ምርት እያመረቱ እንደሆነ ጠቁመዋል።
በበጀት ዓመቱ በከተማዋ ከሚገኙ የቆዳ ኢንዱስትሪዎች 90 ሚሊዮን ዶላር ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅም ነው የተናገሩ፡፡
ኢንዱስትሪዎቹ ባለፉት አምስት ወራት የእቅዳቸውን 73 በመቶ ማሳካት መቻላቸውንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡
የኢንዱስትሪዎችን ምርትና ምርታማነት ማሳደግ በዘርፉ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትሩ፤ ከዚህ አኳያ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡
_ አካባቢህን ጠብቅ፣
_ ወደ ግንባር ዝመት፣
_ መከላከያን ደግፍ።