ሰላምና ፍቅርን የሚሰብከው የ''ድሽታ ግና'' በአል በጂንካ ከተማ እየተከበረ ነው

165

ጂንካ፤ ታህሳስ 01/2014 (ኢዜአ) ሰላምን፣ ፍቅርን እና አንድነትን የሚሰብከው የ''ድሽታ ግና'' በአል በጂንካ ከተማ እየተከበረ ነው።

በደቡብ ኦሞ ዞን ከሚገኙ 16 ብሔረሰቦች አንዱ የአሪ ብሔረሰብ ነው።

በብሔረሰቡ የዘመን ቀመር አቆጣጠር "ሎንጋ'' በተሰኘው የታህሳስ ወር ላይ ሰላምን፣ፍቅርን እና አንድነትን የሚሰብከው የ''ድሽታ ግና'' በዓል በድምቀት ይከብራል።

በአሪ ብሔረሰብ እንደ ዘመን መለወጫ በሚታየው የድሽታ ግና በዓል የተጣሉ የሚታረቁበትና በአከባቢው እርቀ ሰላም የሚወርድበትም ዕለት ሲሆን ይህም አዲሱን አመት በሰላም፣በፍቅርና በአብሮነት ለመቀበል ታስቦ የሚከወን ትውፊት ነው።

ከዚህ ባለፈ በእለቱ የአቅመ ደካሞች ቤት የሚጎበኝበት ሲሆን በተለያዩ ባህላዊ ስነ ስርዓቶች እና ጭፈራዎች እለቱ በድምቀት እየተከበረ ነው።

በጂንካ ከተማ እየተከበረ ባለው የድሽታ ግና በዓል ላይ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል ።

May be an image of 5 people, people standing and outdoors
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም