በመዲናዋ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የታሪፍ መጠን ይሻሻላል

70

ታህሳስ 1/2014 (ኢዜአ) በመዲናዋ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የታሪፍ መጠን እንደሚሻሻል የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ።

የዓለም ዐቀፍ ነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በታህሳስ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ አዲስ የዋጋ ማስተካከያ መደረጉ ይታወቃል።

ይህን ተከትሎ ቢሮው ለኢዜአ በላከው መግለጫ በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት የታሪፍ ማሻሻያ ለማድረግ ጥናት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።

ይህም በቀጣይ ቀናት እንደሚጠናቀቅ ቢሮው አስታውቋል።

ሆኖም የታሪፍ ማሻሻያው ይፋ እስኪሆን ቀደም ሲል በነበረው የታሪፍ ዋጋ አገልግሎቱ እንዲቀጥል አሳስቧል፡፡

በከተማዋ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ አሽከርካሪዎች የታሪፍ መጠኑ ይፋ ሳይሆን ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ ባለማድረግ አገልግሎት በመስጠት ሃላፊነታቸው እንዲወጡ አሳስቧል፡፡

-አካባቢህን ጠብቅ፣

_ ወደ ግንባር ዝመት፣

_ መከላከያን ደግፍ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም