ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ከካናዳው አቻቸው ጀስቲን ቱሩዶ ጋር በስልክ ተወያዩ

72

ታህሳስ 1 ቀን 2014 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ ከካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቱሩዶ ጋር በስልክ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በተፈጠረው ጦርነት ዙሪያ ምክክር አድርገዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ሁለቱ መሪዎች ባሳለፍነው ህዳር 22 ቀን የመከሩባቸው ጉዳዮች በደረሱበት ደረጃ ላይ ሀሳብ ተለዋውጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም