የመደወላቡ ዩንቨርሲቲ ለመከላከያ ሰራዊት 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር የሚገመት የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አደረገ

164

ህዳር 30/2014/ኢዜአ/ የመደወላቡ ዩንቨርሲቲ ለአገር መከላከያ ሰራዊት 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር የሚገመት የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አደረገ፡፡

የዩንቨርሲቲው የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር በዛብህ ወንድሙ፤ ዩኒቨርሲቲው ለሰራዊቱ 2 ሚሊዮን ብር የጥሬ ገንዘብ እና 800 ሺህ ብር የአይነት ድጋፍ አድርጓል ብለዋል።

ከዚህ በፊትም ሁለት መኪና ከነሹፌርና ረዳቶቻቸው ወደ ግንባር በመላክ በሕልውና ዘመቻው ላይ ለተሳተፉ ወገኖች እገዛ እንዲሰጡ ማድረጉን ጠቁመው በቀጣይም ድጋፋችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በሌላ በኩል በአሜሪካ የሚኖሩት አቶ ቢኒያም ሰለሞን እና ቤተሰቦቻቸው ለሰራዊቱ 100 ሺህ ብር ለግሰዋል።

”ከአገር የሚበልጥ ምንም ነገር የለም” በማለት የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ ለማየትና የተቻላቸውን ለማድረግ መገኘታቸውን ገልጸዋል።

በዚህም እርሳቸውና ቤተሰባቸው ለሰራዊቱ አጋርነታቸውን ለማሳየት ድጋፍ ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል።

የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ፤ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።