በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ከኅዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጦር መሣሪያ ምዝገባው እንዲቀጥል ተወሰነ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ መግለጫ ቁ .5

ኅዳር 29 ቀን 2014

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ከዚህ በፊት ባወጣው መመሪያ መሠረት የጦር መሣሪያዎች የምዝገባ ሁኔታን ገምግሟል።

በግምገማው መሠረት ብዙ መሣሪያዎች በየክልሉ የተመዘገቡ መሆኑን በመመልከት ኅብረተሰቡና የጸጥታ ኃይሎች ላደረጉት አስተዋጽዖ ምስጋና አቅርቧል።

የኅብረተሰቡን የተጨማሪ የምዝገባ ጊዜ ጥያቄ ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ከዚህ በፊት የወጣው ትእዛዝ የገጠር አካባቢዎችን ባለማካተቱ የተነሣ፣ የምዝገባውን ጊዜ ማራዘም እንደሚያስፈልግ ዕዙ አምኗል።

በመሆኑም በሁሉም የሀገሪቱ የገጠርና የከተማ አካባቢዎች ከኅዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጦር መሣሪያ ምዝገባው እንዲቀጥል ተወስኗል።

በየደረጃው የሚገኙ የፖሊስ ጽ/ቤቶችም ይሄንን መመሪያ እንዲያስፈጽሙ ታዝዟል።

ይህ መመሪያ በጦር ግንባር የዘመቱና የሚታወቅ የጸጥታ ኃይል እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አካላትን አይመለከትም።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ

_ አካባቢህን ጠብቅ፣

_ ወደ ግንባር ዝመት፣

_ መከላከያን ደግፍ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም