ዓለም አምባ፣ መቅደላና ጎሽሜዳ ከአሸባሪው የሕወሐት ወራሪ ነጻ ወጥተዋል

300

ሰበር ዜና

በአሸባሪው ሕወሐት ተወርረው የነበሩት ቀሪ ከተሞች፣ የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት፣ በዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት በወሰዱት ማጥቃት ነጻ እየወጡ ነው።

ጀግኖቹ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ባደረጉት ማጥቃት በደሴ ግንባር ሐይቅ፣ ቢስቲማ፣ ባሶሚሌ እና ውጫሌ ከተሞች ነጻ ወጥተዋል። ሠራዊቱም ወደ መርሳ እየገሠገሠ ነው።

በተንታ ግንባር በተካሄደው ማጥቃት ዓለም አምባ፣ መቅደላና ጎሽሜዳ ከአሸባሪው የሕወሐት ወራሪ ነጻ ወጥተዋል።

በሁሉም ግንባሮች የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ወደውስጥ ዘልቀው በመግባት የተበታተነውን አሸባሪ ኃይል ቀለበት ውስጥ አስገብተው በመደምሰስ፣ ወራሪው ኃይል የዘረፈውን ንብረት እንዲሁም የያዘውን መሣሪያና ትጥቅ ይዞ እንዳይወጣ እያደረጉት ይገኛሉ።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት።