በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዲስ ክፍለ ክተማ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት 15 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የስንቅ ድጋፍ አደረገ

94

ደብረ ብርሀን፤ ህዳር 29/2014 (ኢዜአ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዲስ ክፍለ ክተማ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት 15 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የስንቅ ድጋፍ አደረገ።
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ሽታዬ መሐመድ በድጋፍ ርክክቡ ሥነ- ሥርዓት ወቅት  እንደገለጹት፤ ድጋፉን ያደረጉት የክፍለ ከተማው  ነዋሪዎችና  ባለሀብቶች ናቸው።

ከድጋፉ ወስጥ ሰንጋ ና የንጽህና መጠበቂያ ቁሶች ይገኙበታል።

የተደረገው ድጋፍ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ከፍ ለማድረግ መሰዋዕትነት እየከፈለ ላለው ለሀገር መከላከያ ሠራዊቱ  ያላቸውን አጋርነት  ለመግለጽና  ለማበረታታት  መሆኑን  አመልክተዋል።

''ጠላቶቻችንን በተባበረ ክንድ መምታት የሁላችንም ድርሻ በመሆኑ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን በመቆም የሀገራችንን  የአሸናፊነት ታሪክ ለመድገም ክፍለ ከተማው የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው'' ብለዋል።

ድጋፍ ቀጣይነት እንዳለውም አስታውቀዋል።

ሲኔር ዋራንት ኦፊሰር ሰለሞን ጌታቸው በበኩላቸው፤  መላው የኢትዮጵያ  ህዝብ  ለሠራዊቱ  ስንቅ በማዘጋጀት እያደረገ ያለው ድጋፍ የሚበረታታ ነው ብለዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ  ግንባር መዝመት   የሠራዊቱን ሞራል ከፍ   በማድረግ  አመርቂ ድሎች እንዲመዘገቡ ማስቻሉን  አብራርተዋል ።

በሀገር ጉዳይ ላይ ድርድርና ቀልድ የለም  ያሉት አቶ ሰለሞን፤ በግንባር የተሰለፈውን   ጠላት ለኛ ተውት፤ የአሸባሪውን የሀሰት ፕሮፖጋንዳና ተባባሪዎችን በመጠቆምና በቁጥጥር ስር እንዲውሉ በማድረግ አግዙን ብለዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ  አስተዳደር የአዲስ ክፍለ ክተማ ነዋሪዎች እስካሁን  ለህልውና  ዘመቻው  ከ72 ሚሊየን ብር በላይ ሀብት በማሰባሰብ ድጋፍ ማድረጋቸውም ተመልክቷል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም