የ’#በቃ’ ‘#NoMore' ዘመቻ አካል የሆነ ሰላማዊ ሰልፍ በአውስትራሊያ ተካሄደ

157

ህዳር 27/2014(ኢዜአ) በደቡብ አውስትራሊያ አዴላይድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የ’#በቃ’ ‘#NoMore' ዘመቻ አካል የሆነ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ።

ሰልፈኞቹ በመልዕክታቸው አሸባሪው ሕወሀትና ተላላኪዎቹ ያደረሱትን ዘረፋና ውድመት፣ አስገድዶ መድፈርና የሰላማዊ ሰዎች ጅምላ ግድያን አውግዘዋል።

ሰለባ ለሆኑ ወገኖችም በተለያየ መንገድ አጋርነታቸውን እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

አንዳንድ ምዕራባውያን ሃገራት በተለይም አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉ ያለውን ያልተገባ ጫና እንዲሁም የዜና አውታሮቻቸው የሚያሰራጩትን አድሏዊና የተዛባ መረጃ እንዲያቆሙ ጠይቀዋል።

ኢትዮጵያ የተመረጠ መንግስት ያላት ሃገር መሆኗን፣ መንግስትን የመቀየር ስልጣን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ በኃያላን ሴራ የሚቀየር እንደሌለ ገልጸው መንግሥት የኢትዮጵያን አንድነት ለማስጠበቅ በሚያደርገው ጥረት ሁሉ ድጋፋቸው እንደማይለየው ገልፀዋል።

ሰልፉን ያስተባበረው የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ማኅበር በደቡብ አውስትራልያ ሲሆን፣ በተያዘው ሳምንት መጨረሻም በሜልቦርን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተመሳሳይ  ትዕይንት ህዝብ ለማካሄድ ማቀዳቸው ከ ኢትዮጵያ ዳይስፖራ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም