በየአካባቢያችን ተደራጅተን የምንጠብቀው ለራሳችን፣ ለቤተሰባችንና ለአገራችን ሰላምና ጸጥታ ስንል ነው

105

አዲስ አበባ ህዳር 25/2014(ኢዜአ) በየአካባቢያችን ተደራጅተን የምንጠብቀው ለራሳችን፣ ለቤተሰባችንና ለአገራችን ሰላምና ጸጥታ ስንል ነው ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ ብሎ በመነሳት በሚችለው አጋጣሚ ሁሉ የጥፋት በትሩን ለማሳረፍ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

የአሸባሪውን እኩይ አላማ በማክሸፍ ኢትዮጵያን ከመበታተን አደጋ ለማዳን ሰራዊቱ በጀግንነት እየተፋለመ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድም በግንባር በመገኘት ሰራዊቱን እየመሩ ይገኛሉ።

በጦር ግንባር እየተደመሰሰ ያለው አሸባሪ ሃይል በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ቢሆንም በጀሌዎቹና ተላላኪዎቹ በአገርና ህዝብ ላይ ችግር እንዳይፈጥር ማህበረሰቡ በየአካባቢው ተደራጅቶ ሰላምና ጸጥታውን እየጠበቀ ነው።

በአዲስ አበባም ነዋሪዎች በየአካባቢያቸው ተደራጅተው ሰላምና ደህንነታቸውን በመጠበቅ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረጉ መሆኑን የኢዜአ ሪፖርተር በምሽት ተዘዋውሮ ተመልክቷል።

በእለቱ በስራ ላይ ያገኘናቸው ነዋሪዎች እንደሚሉት የመዲናዋን ሰላም ለመጠበቅ ከፖሊስ ሥልጠና በመውሰድ እየሰሩ ሲሆን ተጠርጣሪዎች ሲኖሩም ለፖሊስ ያስረክባሉ።

በየአካባቢያችን ተደራጅተን የምንጠብቀው ለራሳችን፣ ለቤተሰባችንና ለአገራችን ሰላም ስንል ነው ብለዋል ነዋሪዎቹ።

ወይዘሮሰርካለምዘውዴ በሰጡትአስተያየትየሰፈሩ ነዋሪ በሁለት ፈረቃ በመከፋፈል የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ በንቃት እየጠበቀ ነው ብለዋል፡፡

ወይዘሮ ትዝታ ፈለቀ በበኩላቸው ህብረተሰቡ ወጣት ሳይል ሽማግሌ በመደራጀት ሳይሰላች ግዴታዬ ነው በሚል ስሜት አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ ላይ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የጥበቃ ስራው ላይ ሻንጣ የያዙ ሰዎች ካሉ በመፈተሽ መታወቂያም ያልያዘ አጠራጣሪ ሰው ካጋጠመም ለፖሊስ አሳልፎ በመስጠት የአገራቸው፣የራሳቸውና የቤተሰባቸውን ደህንነት በመጠበቅ ላይ መሆናቸውን የገለፁት አቶ ሁሴን አንደርባ ናቸው፡፡

የአገር መከላከያ ሠራዊትና ሌሎች የጸጥታ አካላት የኢትዮጵያን ክብር እያስጠበቁ ባለበት ወቅት እኛም አካባቢያችንን ብሎም ከተማችንን በመጠበቅ የድርሻችንን እየተወጣን ነው ብለዋል።

ህዝቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ ከፖሊሶች ጋር  ቀረቤታን በማጠናከር ስልጠና በመውሰድ አካባቢያቸውን በመጠበቅ ላይ እንደሚገኙ ወጣት አይረዲን አንዋር ይናገራል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የዘማች ቤተሰቦች በኢኮኖሚ ድጋፍ እንዲያገኙ የማስተባበር ስራም እንዲሁ፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም