የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚያወግዝ ሰልፍ በባህርዳር እየተካሄደ ነው

77

ባህር ዳር ህዳር 24.2014 (ኢዜአ ) በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የውጭ ጣልቃ ገብነትንና ጫናን የሚያውግዝ ሰልፍ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።
የ1ኛና 2ኛ ደረጃ ተማሪዎችና መምህራን እያካሄዱት ባለው ሰልፍ ምእራባዊያን በኢትዮጵያና በኤርትራ ላይ እያደረሱ ያለውን  ጣልቃ ገብነት የሚያወግዝ ድምጽ እየተስተጋባ ነው።

ሰልፈኞቹ ቢቢሲና ሲ ኤን ኤን የሃሰት መረጃ ማስተላለፍ ያቁሙ፣ በሃሰት መረጃ የሚፈርስ ሃገር የለም፣  ኢትዮጵያ አትፈርስም፣ ኢትዮጵያ በጀግኖቿ አፍራ አታውቅምና ግድቡ ተሞልቷል የሚሉ መፈክሮች በማደሰማት ላይ ናቸው።

ኢትዮጵያ ታሸንፋለች፣አሜሪካ በዲሞክራሲ ስም መነገድ ታቁም ''no more'' ''በቃ'' የሚሉ መፈክሮችም በሰልፈኞቹ እየተስተጋቡ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም