አሸባሪው ህወሓት በደብረሲና ከተማ ያሉ ጤና ጣቢያዎችንና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሙሉ በሙሉ አውድሟል

ህዳር 23 ቀን 2014 (ኢዜአ) አሸባሪው ህወሓት በደብረሲና ከተማ ያሉ ጤና ጣቢያዎችንና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሙሉ በሙሉ ማውደሙ ተገለጸ።

ቡድኑ ከተቋማቱ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችና መድሀኒቶችን ዘርፏል፤ መውሰድ ያልቻለውን ደግሞ ለአገልግሎት እንዳውል አድርጎ አበላሽቷል።የጣርማበር ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ወንድም ተሰማ እንዳሉት፤ የደብረሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከ100 ሺህ በላይ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል የተሟላ ግብዓት ነበረው።

ይሁን እንጂ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በወረዳው ያሉ አራት ጤና ጣቢያዎችን ጨምሮ የደብረሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን ሙሉ በሙሉ አውድሟል። በጤና ተቋሞች የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶች፣ የላቦራቶሪ እቃዎች፣ መድሀኒቶች በሙሉ ተዘርፈዋል፣ ቀሪዎቹን ከጥቅም ውጭ አድርጓቸዋል፡፡

አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ሁሉም የጤና ተቋማት አገልግሎት መስጠት አይችሉም ነው ያሉት፡፡በዚህም ከእነርሱ ጥይት የተረፈውን በህክምና እጦት እንዲሞት በማድረግ ለህዝብ ያላቸውን ጥላቻ በተግባር አሳይተዋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም