የወንጪ ሃይቅን የ2021 የዓለም ምርጥ የቱሪዝም መንደር ሆኖ መመረጡን አስመልክቶ የማብሰሪያ መረሃ ግብር እየተካሄደ ነው

174

ህዳር 23/2014( ኢዜአ) የተባበሩት መንግስታት የዓለም የቱሪዝም ደርጅት የወንጪ ሃይቅን የ2021 ምርጥ የቱሪዝም መንደር አድርጎ መምረጡን አስመልክቶ የማብሰሪያ መረሃ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡

የተባበሩት መንግስታት የዓለም የቱሪዝም ደርጅት የወንጪ ሃይቅን የ2021 ምርጥ የቱሪዝም መንደር አድርጎ መምረጡ ይታወቃል፡፡

ይህን ተከትሎም ድርጅቱ ዛሬ በማድሪድ ከተማ በሚያካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ የወንጪ ሃይቅን የ2021 የቱሪዝም መዳረሻ መሆኑን የሚያበስር ሽልማት ያበረክታል፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትሯ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊን ጨምሮ የክልልና የፌደራል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የዘርፉ ባለድርሻ በተገኙበትም ሚያበስር መርሃ-ግብር በወንጪ ሃይቅ  እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የወንጪ ሃይቅ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ይፋ በተደረገው “የገበታ ለአገር” መርሃ ግብር  የቱሪስት መዳረሻ ሆነው እንዲለሙ ከተመረጡ ሶስት አካባቢዎች አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡