የክፍለ ከተማው አመራሮችና የጸጥታ አካላት በቀርሳ ኮንቶማ የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ሰበሰቡ

137

አዲስ አበባ፣ ህዳር22/2014 (ኢዜአ) በአዲስ አበባ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አመራሮችና የጸጥታ አካላት በቀርሳ ኮንቶማ የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ሰበሰቡ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለህልውና ዘመቻው በገንዘብ እና ቁሳቁስ ከሚደርገው ድጋፍ በተጨማሪ የደም ልገሳ በማድረግ እንዲሁም የዘማች ቤተሰቦችን በመደገፍ ላይ ይገኛል።

በዛሬው እለትም የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አመራሮች እና የጸጥታ አካላት በክፍለ ከተማው በቀርሳ ኮንቶማ አካባቢ በመገኘት የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ሰብስበዋል።

በሰብል ስብሰባው ላይ ያገኘነው ወጣት መስፍን ለማ፤ ለህልውና ዘመቻው ወንድሙ ወደ ግንባር በመዝመቱ የቤተሰቡ ሰብል በመሰብሰቡ መደሰቱን ይናገራል።

በሰብል አጨዳው ላይ ያገኘናቸው ዋና ሳጅን ጉዲሳ ፈይሳ እና ዋና ሳጅን ታረቀኝ ተክሌ የአካባቢውን ሰላም ከማስከበር ጎን ለጎን ማህበረሰቡን በማገዝና በመደገፍ ላይ በመሆናቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ነጻነት ዳባ፤ በቀርሳ ኮንቶማ የተጀመረው የዘማች ቤተሰቦች ሰብል አጨዳ በሌሎች አካባቢዎችም ይቀጥላል ብለዋል።

በክፍለ ከተማው ማህበረሰቡ በሰብል አጨዳ፣ በመሰብሰብና በሰብል መውቃት እየተባበረ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም