የመዲናዋ የተለያዩ ተቋማት ለመከላከያ ሠራዊት ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

100

አዲስ አበባ ህዳር 22/2014 (ኢዜአ) የአዲስ አበባ ሴቶች ህጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ፣ የሴቶች ማኅበር፣ የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ እና የምገባ ኤጀንሲ ለመከላከያ ሠራዊት ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አደረጉ።
ድጋፉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለመከላከያ ሚኒስቴር አስረክበዋል።

ተቋማቱ ከመዲናዋ ሁሉም ክፍለ ከተሞች ከሚገኙ የተለያዩ አካላት ያሰባሰቡትን የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ነው ያስረከቡት።

ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመተውን የቁሳቁስ ድጋፍ ያበረከቱት የአዲስ አበባ ሴቶች ህጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ፣ የሴቶች ማኅበርና የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ በጋራ ነው።

የምገባ ኤጀንሲ ደግሞ 5 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር እንዲሁም በተማሪዎች ምገባ ስራ የተሰማሩ እናቶች ከደመወዛቸው 500 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል።

ድጋፉን ያስረከቡት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በስንቅ ዝግጅት እየተሳተፉ ያሉ እናቶችን አበረታተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም