ኢትዮጵያን ለመታደግ በጀግንነት መስዋዕትነት መክፈል ክብር ነው

88

አዲስ አበባ፣  ህዳር 21/2014(ኢዜአ) “ኢትዮጵያን ለመታደግ በጀግንነት መስዋዕትነት መክፈል ክብር ነው” ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡

ከንቲባዋ በመከላከያ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመገኘት በህልውና ዘመቻው ጉዳት ለደረሰባቸው የሰራዊት አባላት የምሳ ግብዣ አድርገዋል፡፡

ከንቲባዋ በዚህ ወቅት “ኢትዮጵያን ለመታደግ በጀግንነት መስዋዕትነት መክፈል ክብር ነው፤ ታሪክ ሰርታችሁ ታሪክ እንድንጽፍ ስላደረጋችሁን ምስጋና ይገባችኋል” ሲሉም  ሰራዊቱን አበረታተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 300 የህክምና ባለሙያዎች በሆስፒታሉ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረጉንም ገልጸዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ እስካሁን ባለው ሂደት ለሆስፒታሉ ከ21 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉንም ጠቁመዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የህልውና ዘመቻው በድል እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡