አካዳሚው ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ15 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አደረገ

75

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21/2014(ኢዜአ)  የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ለተፈናቀሉ ወገኖች 15 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉን የአካዳሚው ፕሬዝዳንት ዶክተር ምህረት ደበበ፤ ለአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ በዛሬው እለት አስረክበዋል።

ከአጠቃላይ ድጋፉ የአካዳሚው ሰራተኞች የወር ደሞዛቸውን በመለገስ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን  ብር ሲያበረክቱ ቀሪውን አካዳሚው መለገሱ ታውቋል።