"አሁን ተማሪዎቼ ስለተመረቁ ለመዝመት ዝግጁ ነኝ"

68

ሚዛን አማን (ኢዜአ) ህዳር 18/2014 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ "ግንባር ላይ እንገናኝ'' ሲሉ ላቀረቡት ሀገራዊ ጥሪ "አሁን ተማሪዎቼ ስለተመረቁ ለመዝመት ዝግጁ ነኝ" ሲሉ ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሠራተኞች መካከል የሥነ-ሕይወት ምህሩ አንዱ ናቸው።
የአንድ ሀገር የልማት የዕድገትና የብልፅግና ራዕይ እውን የሚሆነው ጥራት ባለው የትምህርት ሥርዓት ሲደገፍ ብቻ ነው። ስለሆነም ሙያዊ ዕውቀትንና ክህሎትን ከዘመኑ የሣይንስና ቴክኖሎጂ ውጤቶች ጋር ራሱን አዋህዶ እያዘመነ የሚሄድ የትምህርት ሥርዓት የሁሉም ነገር መሰረት ነው። ትምህርት ለሀገር ሁለንተናዊ ልማትና ዕድገት የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ ደግሞ የዘርፉ ግንባር ቀደም ተዋኒያን የሆኑት መምህራን የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ።

በየትኛው ደረጃ የሚገኙ መምህራን ትምህርት ለሀገር ሁለንተናዊ ልማትና ዕድገት  የሚጠበቅበትን የላቀውን አበርክቶውን እንዲወጣ መልከ ብዙና ዘርፈ ብዙ ኃላፊነት እንዳለባቸው ሁሉም የሚያውቀው፤ ፀሐይ የሞቀው ሀቅ ነው። በሥነምግባር የታነጹ፤ ከሁሉም በላይ ሀገራቸውንና ሕዝባቸውን የሚያስቀድሙ፣ ከእኔ ይልቅ ሀገሬ ትቅደም፣ ከራሱ ይልቅ እኔን አስቀድሞ ለዚህ ያበቃኝ ሕዝቤ ይልማ፣ ይደግ፣ ይመንደግ ይበልፅ በሚል የለውጥ አስተሳሰብና አመለካከት የበለፀጉ ራሳቸው በሣይንስና ቴክኖሎጂ ውጤቶች ዕውቅት ክህሎት አዳብረው ያበለጸጉ፤ ዘመን ያፈራቸው የሣይንስና ቴክኖሎጂ ውጤቶች ለሀገርና ለሕዝብ ጥቅም ብቻ እንዲውሉ የሚተጉ ሀገር  ወዳድና ተረካቢ ዜጎችን ማፍራት ከመምህራን ሙያዊ ኃላፊነቶችና የዜግነት ግዴታዎች መካከል በግንባር ቀደም ይጠቀሳሉ።

መምህራን ሀገር ወዳድና ተረካቢ የተማረ ዜጋ በማፍራት ሙያዊ ኃላፊነታቸውንና የዜግነት ግዴታዎቸውን የሚወጡት ሰለም ሲኖር ብቻ እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉ። ስለዚ ሀገር ሰላምና ደህንነት ቅድሚያ መስጠት ከሁል ጊዜ ተግባራቸው አንዱ ነው።

አሸባሪው ሕወሓት ኢትዮጵያን አፍርሶ ኢትዮጵያውያንን የመበታተን የዘመናት ውጥኑን እውን ለማድረግ የጋረጠውን ወቅታዊ የሕልውና አደጋ በተባበረ ክንድ ለመቀልበስ ኢትዮጵያ በመሪዋ በኩል ጥሪ አቅርባለች። ለዚህ ጥሪ መላው ኢትዮጵያውያን ፈጣን አዎንታዊ ምላሽ ሰጥተዋል። የክተት ጥሪውን ተቀብለው ከአውደ ውጊያው ስፍራ ፈጥኖ ለመድረስ ዝግጁነታቸውን ገልጸው ተግባራዊ እንቅስቃሴ ጀምረዋል። ለእናት ሀገር ጥሪ ፈጣን ምላሽ ከሰጡት በየደረጃው ከሚገኙ የትምህርት ተቋማት ማህበረሰብ መካከል የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ  መምህራንና ሠራተኞች ይገኙባቸዋል።

ረዳት ፕሮፌሰር አክሊሉ አይዛ ይባላሉ። የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ሕይወት ትምህርት መምህር ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ  "ግንባር ላይ እንገናኝ'' ሲሉ  ላቀረቡት ሀገራዊ  ጥሪ "አሁን ተማሪዎቼ ስለተመረቁ ለመዝመት ዝግጁ ነኝ" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። እንደ እሳቸው ሃሳብ ወደ ግንባር አቅንተው አውደ ውጊያውን የሚቀላቀሉት ገና የሕልውና ዘመቻው ሲጀመር ነበር። ነገር ግን የሚያማክሯቸው የሁለተኛ ዲግሪ መርሃ ግብር የማሟያ የጥናት ጽሁፍ የሚሰሩ ተማሪዎች ነበሩ። በዚህ ምክንያት እንዳሰቡት ፈጥነው የሕልውና ዘመቻውን መቀላቀል አልቻሉም። አሁን ግን ሲከታተሏቸው የነበሩ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ስላጠናቀቁ ከአሰቡበት የሚገታቸው አንዳች ነገር የለም።

እንደ ረዳት ፕሮፌሰር አክሊሉ ገለጻ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የሕልውና ጦርነቱን ለመምራት ወደ ግንባር ማቅናታቸው "እኔስ ለሀገሬ" ብለው እንዲነሳሱ አድርጓቸዋል። የዶክተር ዐብይ መዝመትን ተከትሎ በትግሉ ሜዳ ጠላትን ለመፋለም ዝግጁ መሆናቸውንም ለዩኒቨርሲቲው የበላይ አመራር አሳውቀዋል።

"ኢትዮጵያ የምትኖረው እኔና ልጆቿ ዋጋ መክፈል ስንችል ነው የሚል ፅኑ እምነት አለኝ፤ የቆሰለችው ሀገራችን ቁስሏን አክሞ የሚያድን ልጅ ትሻለች"። አሁን ወደግንባር ለመዝመት ዝግጁ ነኝ ይላሉ።

አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን እየወጋ ያለው ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር አብሮ ነው። በመሆኑም ሁሉም ኢትዮጵያዊ  ይህን የሽብር ቡድኑን እኩይ ዓላማ ተረድቶ ሀገሩን ከብተና ለመታደግ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። ይህን ሀገራዊ አስተዋጽኦውን  አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

የዩኒቨርሲቲው የግዥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ በበኩላቸው ለመከላከያ ሠራዊት ከደመወዛቸው ቢለግሱም ሀገር ከገጠማት ችግር አንጻር ሲታይ በቂ አይደለም ይላሉ።በዓድዋ ጦርነት ኢትዮጵያዊያን በሕብረት ዘምተው ለድል መብቃታቸውን አስታውሰው፣ "የዚህ ዘመን ባለአደራ እኛ እንደመሆናችን ለመዝመት ቆርጫለሁ" ሲሉ ነው የሕልውና ትግሉን ለመቀላቀል ዝግጁ መሆናቸውን ያረጋገጡት። "ጠቅላይ ሚንስትሩ ያሳዩንን የሀገር ፍቅር ስሜት ወደ እኛ በማጋባት ለሀገር የሚከፈለውን መስዋዕትነት መክፈል አለብን" ሲሉም አክለዋል።

"ኢትዮጵያ በታሪኳ ሽንፈትን አታውቅም" ያሉት አቶ ገዛኸኝ፣ አሁን በአሸባሪው ህወሓት የጦርነት ትንኮሳ ኢትዮጵያ ፈጽሞ ወደማትፈልገው ጦርነት ውስጥ ገብታለች። የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ይህን ሳይፈልጉ ተገደው የገቡበት ጦርነት በአጠረ ጊዜ ውስጥ በድል ለማጠናቀቅ ሁሉን አቀፍ ትግል እያደረጉ ነው። ይህ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በግንባር እየመሩት ያለው የሕልውና ጦርነት እጅግ በአጠረ ጊዜ በድል እንዲጠናቀቅ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እያደረገ ያለውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ወይዘሮ ገነት መኩሪያ ከዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ሠራተኛ መካከል አንዷ ናቸው።  እሳቸውም "ሀገራችን ከገባችበት አጣብቂኝ እስክትወጣ ድረስ ከመከላከያ ጎን በመቆም ድጋፌን እቀጥላለሁ" ነው ያሉት። "የውጭ ሀገር ጣልቃ ገብነት ኢትዮጵያን ሆነ ብሎ ለመጉዳት የተሴረ በመሆኑ አጥብቄ እቃወማለሁ" ሲሉም አክዋል።"በጦርነቱ ሀገራችን ታሸንፋለች፤ የጠቅላይ ሚንስትራችንን ምሳሌነት በመከተል እኛም እንዘምታለን" ሲሉም አስተያየታቸውን ቋጭተዋል።

የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሠራተኞች ሁሉም ነገር ከሀገር ደህንነት በኋላ የሚደርስ በመሆኑ ለሀገር ቅድሚያ ሰጥተው በአሸባሪው ህወሓት የተጋረጠውን ወቅታዊ የሕልውና አደጋ ለመቀልበስ መቁረጣቸውን አረጋግጠዋል። ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ ደም ተጠብቃ እስካሁን መቆየቷን አስታውሰው፣ ዛሬም ኢትዮጵያን ለመድፈር የመጣን ጠላት ለመደምሰስ ሁሉም በአንድነት መነሳት እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አህመድ ሙስጠፋ በግንባር ለመዝመት ለተቋሙ ደብዳቤ ያስገቡ የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች መኖራቸውን ገልጸው፤ ዩኒቨርቲው ፍላጎት ወደ ግንባር የሚዘምቱ ማህበረሰቦቹን ቤተሰቦቻቸውን አስፈላጊውን ድጋፍና እንክብካቤ እንደሚያደርግ አረጋ ሚዛን አማን (ኢዜአ) ህዳር 18/2014 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ "ግንባር ላይ እንገናኝ'' ሲሉ ላቀረቡት ሀገራዊ ጥሪ "አሁን ተማሪዎቼ ስለተመረቁ ለመዝመት ዝግጁ ነኝ" ሲሉ ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሠራተኞች መካከል የሥነ-ሕይወት ምህሩ አንዱ ናቸው።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አህመድ ሙስጠፋ በግንባር ለመዝመት ለተቋሙ ደብዳቤ ያስገቡ የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች መኖራቸውን ገልጸው፤ ዩኒቨርቲው ፍላጎት ወደ ግንባር የሚዘምቱ ማህበረሰቦቹን ቤተሰቦቻቸውን አስፈላጊውን ድጋፍና እንክብካቤ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም