በጎንደር ከተማ አስተዳደር አስተባባሪነት ‘ኢትዮጵያ ትጣራለች’ በሚል በተካሄደው መርሃ ግብር ላይ 160 ሚሊዮን ብር ተሰበሰበ

86

ህዳር 19 ቀን 2014 (ኢዜአ) በጎንደር ከተማ አስተዳደር አዘጋጅነት በአዲስ አበባ በተካሄደው ‘ኢትዮጵያ ትጣራለች’ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ላይ 160 ብር ተሰበሰበ።

ባለሃብቱ ወርቁ አይተነው 50 ሚሊየን ብር፣ ጎመጁ ኦይል ኢትዮጽያ 20 ሚሊየን ብር፣ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ 5 ሚሊዮን ብር፣ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር፣ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ 2 ነጥብ 25 ሚሊዮን ብር፣ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ 3 ሚሊዮን ብር፣ ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ 1 ሚሊዮን ብር፣ ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር፣ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ 1 ሚሊዮን ብር ለመለገስ ቃል ገብተዋል።

በመርሃ ግብሩ በርካታ ግለሰቦች፣ ተቋማት እና ድርጅቶች በርካታ ገንዘብ ለመለገስ ቃል ገብተዋል።

ከገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር የተገኘው ገቢ ለመከላከያ ሠራዊቱ፣ ለአማራ ልዩ ሃይል፣ ለሌሎች የጸጥታ አካላት እንዲሁም ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል መሆኑንም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም