ቤታቸውን ሸጠው ለመከላከያ ሰራዊት የለገሱት እናት

338

ህዳር 17/2014 (ኢዜአ) በአዲስ አበባ የሚኖሩት ወይዘሮ ቦጋለች ከበደ፤ የመኖሪያ ቤታቸውን ሸጠው 2 ሚሊዮን ብር ለአገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አድርገዋል።

አገር ከሌለ ሁሉም ነገር የማይቻል በመሆኑ በቤት ለመኖር ቅድሚያ አገርን በክብር ማኖር ይገባል በማለት ቤታቸውን ሸጠው ለኢትዮጵያ ህልውና እየተፋለመ ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊት ለግሰዋል።

የአገር ህልውናን ለማስጠበቅ እየተደረገ ባለው ዘመቻ ህዝቡ ከጫፍ ጫፍ በመንቀሳቀስ በመዝመትና በመደገፍ የጎላ እስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል።