ግለሰቡ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን ለሰራዊቱ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሶችን አበረከቱ

67

ጎንደር ህዳር 16/2014 (ኢዜአ ) አቶ ተስፋሁን ደረጃ በውጪ ከሚኖሩ ቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን 200 ሺህ ብር የሚገመቱ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሶችን በግንባር ለሚፋለመው ሰራዊት አበረከቱ።
በአዲስ አበባ የሚኖሩት ግለሰቡ ድጋፉን  ያበረከቱት  ዛሬ በጎንደር ከተማ በመገኘት ነው ።

የሀገርን ህልውና ለማስጠበቅ መንግስት መላ ህዝቡና ሰራዊቱ  እያደረጉት ያለውን ተጋድሎና ርብርብ አቅም በፈቀደ መጠን መደገፍ የማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ግዴታው ነው።

ሀገር የሁሉም ዜጎቿ መኖሪያና መከበሪያ በመሆኑዋ ለሀገራችን ሉአላዊነትና ነጻነት ቅድሚያ በመስጠት የቤተሰብ አባላቱ በግንባር ለሚዋደቀው የፀጥታ ሃይል ድጋፉን ማበርከታቸውን ተናግረዋል፡፡

ከድጋፉም መካከል ለሰራዊቱ የውሃ መያዣ የሚውሉ ኮዳዎች፣ እሽግ ውሃ፣ አልባሳት፣ ጫማዎች፤ የለስላሳ መጠጦችና ቴምር ይገኙበታል።

በቀጣይም ሰራዊቱ የሽብር ቡድኑን ደምስሶ ለኢትዮጵያ ህዝብ ድል እስኪያበስር ድረስ  ድጋፋቸውን አጠናክረው ለመቀጠል  ቃል ገብተዋል፡፡

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዘውዱ ማለደ፤  የቤተሰብ አባላቱ ያደረጉትን ድጋፍ የጸጥታ አካል በፍጥነት እንዲደርስ እንደሚደረግም አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም